Thursday, 17 June 2021

ስለ ኮሚሽኑ ( /ቤቱ) ታሪካዊ ዳራ

የኤፌዴሪ ህገ-መንግስት   መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንፁህና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው ጥረት ማድረግ እና ማንኛውም ኢኮሚያዊ ልማት አካባቢ ደህንነትን የሚያናጋ መሆን እንደሌለበት እንዲሁም  ማንኛውም ሰው ጤናማና ንፁህ አካባቢ የመኖር መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡  ይሄንን መብትና ግዴታ  ለማስከበር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 9/1987 ራሱን ችሎ በፌደራል የመንግስት መስሪያቤትነት ተቋቋመ፡፡

ባለስልጣኑ የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንቅስቃሴዎች የሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ የሰውን ልጅ ደህንነት ለመንከባከብና የአካባቢ ሃብቶችን ዘላቂነት ባለው መንገድ ለማስጠበቅ ታልሞ በአንድ ሥራ አስኪያጅ በአንድ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና  120 በላይ  ሰራተኞች መዋቅር በአዋጁ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተጣለበትን ሐላፊነት ሲወጣ ቆይቷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዚህ አደረጃጀት  18 ዓመታት የአካባቢ ፖሊሲና ህጎችን፣ የተፈጥሮ ሃብት ስነ- ህይወታዊ ስርዓቶችን የሚያስጠብቁ ደረጃዎችን በማውጣት፣ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማን በመከታተል እና የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት ሀገሪቱ የተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች በስራ ላይ መዋላቸውን ከትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

እንዲሁም ለአየር ንብረት ለውጥ ለሚሰጠው ሀገራዊ ምላሽ  በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲያስተባብር  ለባለስልጣን  መስሪያ ቤቱ  ኃላፊነት ተሰጥቶት ስለነበር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ራዕይ፣  ስትራቴጅ የማስፈፀሚያ ስልት፣  የመማጣጣሚያ መርሀግብር እና የስርየት እርምጃዎች ስርዓት እንዲኖር ያደረገ ሲሆን በተለይም የአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድርን በመምራትና በማስተባበር እጅግ አመርቂ ስራን ሰርቷል፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ራዕይን ተግባራዊ ለማድረግ ከተመረጡ አራት ምሰሶዎች አንዱ ደን ነው፡፡የደን ልማትን ለማስፋፋትና አያያዙን ለማሻሻል ራሱን የቻለ ኃላፊነት የሚወስድ ተቋም በማስፈለጉ   ሀምሌ 22/2005 . የኢ.... አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ 691/2003  አንቀፅ  9 ላይ አዲስ ንዑስ አንቀፅ 21 በመጨመር በአዋጅ 803/2005 የፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንና ከግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የደን ንዑስ ዘርፍን በማቀናጀት የአካባቢና የደን ሚኒስቴር እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

የአካባቢና የደን ሚኒስቴር  አንድ ሚኒስትር 'ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሃያ ሶስት ዳይሬክቶሬቶች  370 በላይ የሰራተኞች መዋቅር ተዘርግቶ የአካባቢና የደን አያያዝ ልማትና አጠቃቀምን በማረጋገጥ 2017 . ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን የገነባች መካከለኛ ገቢ ያላት ሃገር ሆና ማየት የሚለውን ግብ ጥሎ በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባራት ለመወጣት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በደን ዘርፉ የተቋቋሙ ዳይሬክቶሬቶች የደን መርሀግብሮችን የመዘርጋት' ምርት ሰጪ ደኖች ልማት ማስፋፋት 'የደን ምገዝብና ኢንቨንተሪ ማደረግ 'ሳይንሳዊ የችግኝ ተከላ እንዲካሄድ የማገዝ 'ለካርቦን ገበያ ድጋፍ ማፈላለግና  የተመናመኑ ደኖችን ለመስጠበቅ የእናት ዛፍ ዘር አመራረጥና አያያዝ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

የአካባቢ ዘርፉ ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ የተለያዩ የአለም አቀፍ ስምምነቶችና ሌሎች ህጎችን በማዘጋጀት፤ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነዶችን ግምገማ በማድረግ ግብረመልስ በመስጠት' የወጡ የተለያዩ የአካባቢ ህጎች አተገባበር በመቆጣጠር፤ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ገንዘብ በማሰባሰብ ቴክኖሎጅዎችን በመቀመርና በማስፋት፤ የፕሮጅክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ በማድረግ  እንዲሁም ለህብረተሰቡ ስለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንዛቤ በመፍጠር መስሪያቤቱ የተጣለበትን ሃገራዊ ኃላፊነት ተወጥቷል፡ (የአካባቢ፣የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር እና ኮሚሽን ታሪክ ይጨመራሉ)

 

 

 

 

 

የኮሚሽኑ አድራሻ

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል በስተጀራባ ኢሚግሬሽን ቢሮ ወረድ ብሎ፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9

ስልክ፡ +251 (0)11-170-4038/4150

ፋክስ፡ +251 (0)11-170-4158/ 45

ኢመይል   efcccethiopia@gmail.com

ቲውተር   https://twitter.com/efccc14

ፌስቡክ   https://www.facebook.com/MefEth/

ቴሌግራም   https://t.me/efcccethiopia

..      12760

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ